
የካቲት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት ስድስት ወራት በኢትዮጵያ ላይ የተሰነዘሩ ከ3 ሺህ 400 በላይ የሳይበር ጥቃቶችን መመከት መቻሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በሳይበር ደኅንነትና ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ኢትዮጵያ 96 በመቶ የሳይበር ጥቃትን የመመከትና የመቋቋም አቅም መገንባት ችላለች፡፡
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት በኢትዮጵያ ላይ የተሰነዘሩ ከ3 ሺህ 400 በላይ የሳይበር ጥቃቶችን መመከት ተችሏል ነው ያሉት፡፡
ጥቃቶቹ ተፈጽመው ቢኾን ኖሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ አደገኛ ሁኔታ ይፈጥሩ እንደነበርም ነው የገለጹት፡፡
ከጥቃት ሙከራዎች መካከል 33 በመቶ የሚሆነው የመሰረተ ልማት ቅኝት፣ 25 በመቶ የድረ-ገጽ ጥቃት፤ 21 በመቶ ሰርጎገብነት፤ 19 በመቶ የማልዌር ጥቃት እንዲሁም የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾችን መጠለፍ እና የኦንላይን ማጭበርበር መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የፋይናንስ ተቋማት፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ አምራች ተቋማት እና ሚዲያዎች ደግሞ ዋነኛዎቹ የጥቃት ዒላማዎች መኾናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
በተጨማሪም ጥቃት የደረሰባቸውን በፍጥነት ወደ አገልግሎት መመለስ መቻሉንም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
“የሳይበር ደኅንነት ጥቃት የዓለማችን ቀጣዩ ወረርሽኝ ነው” ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃት መከላከል ላይ ትኩረት አድርጋ እየሠራች መኾኑን አብራርተዋል፡፡
እያንዳንዱ ግለሰብ የሳይበር ሕግጋትን አክብሮ በመጠቀም ለሳይበር ጥቃት መከላከል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የዲጂታል ሉዓላዊነት የኹሉም ሀገራት ስጋት በመኾኑ ሚዲያዎች ጉዳዩን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን በስፋት እንዲሠሩም ጠይቀዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/