የታዳጊው ወጣት ሰናይ ተግባር – በደባርቅ

271

ባሕር ዳር: የካቲት 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ታዳጊ ወጣት ታምራት ቀፀላ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ከተማ ነው።

ዕድሜው 17 ዓመት ሲሆን የ11ኛ ክፍልም ተማሪ ነው። ለቤተሰቦቹ ደግሞ ብቸኛ ልጅ ነው። እነሱንም የሚያስተዳድረው በጫማ ማስዋብ ሥራ ነው።

ወጣት ታምራት ቀፀላ፣ አሸባሪው የትህነግ ቡድን ደባርቅን እና ዳባት ወረዳዎችን ቆርጦ በጎንደር በኩል ለማምለጥ ባሰበበት ጊዜ በጭና አካባቢ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከስንቅ እስከ ተተኳሽ ድረስ በመሸከም ድጋፍ አድርጓል።

“ሰራዊቱ ለመውጣት አይደለም ለመመልከት የሚከብዱ ረጃጅም ተራራዎችን ነጭ ላቡን እና ደሙን እያፈሰሰ በመውጣት ጠላት ሲደመስስ በአካል ተገኝቼ አይቻለሁ” ሲልም ተናግሯል።

ይህን ከተመለከትኩ ጊዜ ጀምሮ ለእኔ ሲል በምንም በማንም የማይተካውን ህይወቱን ለሚከፍልልኝ ጀግናው ሠራዊታችን ባለኝ ነገር ለመደገፍ ወሰንኩ ይላል ታዳጊ ወጣት ታምራት።

እኔን እና ቤተሰቦቼን የማስተዳድረው በጫማ ማስዋብ ሥራ ነው። አቅሜ የሚፈቅደው ደግሞ ለጀግናው ሠራዊታችን ጫማቸውን በነፃ መቀባት ነው። በዚህም በምሰራበት አካባቢ “ለሀገር መከላከያ ሠራዊታችን በነፃ ጫማ እንቀባለን” ብዬ ፅፌ ለሠራዊቱ በነፃ ጫማ እቀባለሁ ብሏል።

“ከዚህም በተጨማሪ በእየለቱ ከማገኘው ገቢ 15 ከመቶውን በመቀነስ በየወሩ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እደግፋለሁ። አሁንም ይህን ተግባር አጠናክሬ እቀጥላለሁ” ሲል ተናግሯል።

የደባርቅ ከተማ ነዋሪ አቶ ጌታቸው አሰፋ ስለ ታዳጊው ወጣቱ ታምራት ቀፀላ እንደተናገሩት፣ ለሠራዊቱ ጫማቸውን በነፃ በመቀባቱ የአካባቢው ነዋሪ የእሱን ሰናይ ተግባር ተመልክተው በቻሉት መንገድ ሁሉ ጀግናውን ሠራዊት እንዲደግፉ ከፍተኛ የሆነ መነቃቃትን የፈጠረ ጀግና ወጣት ነው ሲሉ ተናግረዋል። መረጃው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ነው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአሸባሪው ትህነግ በአፋር ክልል እያደረሰ ያለውን ጥቃት መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ።
Next article5ሺህ ሰዎች የተገኙበት የፍቅር ምሳ ግብዣ በደሴ ከተማ አይጠየፍ አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡