አሸባሪው ትህነግ በአፋር ክልል እያደረሰ ያለውን ጥቃት መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ።

178

ባሕር ዳር: የካቲት 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ በአፋር ክልል ክልበቲ ረሱ ዞን እያደረሰ ያለውን ጥቃት አጠናክሮ መቀጡን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ በአፋር ክልል ክልበቲ ረሱ አካባቢ ባደረሰው ወረራና ጥቃት የአበአላ፣ ኮናባ፣ እሪፕቲ ፣ መጋሌ እና በረሃሌ ወረዳ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡

አሁን ላይም በሽብር ቡድኑ ጥቃት የተፈናቀሉ ዜጎች በኮሪ ወረዳ ጉዋህ ቀበሌ ተጠልለው እንደሚገኙ ፋብኮ ዘግቧል።

የሽብር ቡድኑ በማኅበረሰቡ ላይ እየፈጸመ ባለው የከባድ መሳሪያ ጥቃትም ለከፍተኛ ሰቆቃ መዳረጋቸውን ነው ተፈናቃዮቹ የገለጹት።

ወራሪው ቡድኑ እያደረሰ ባለው ጥቃት ቤተሰብ ከቤተሰቡ ጋር ተለያይቶ መገናኘት እንዳይችል ማድረጉንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

ወራሪው ቡድን እያደረሰ ያለውን ጥፋት መንግሥት እና የሚመለከተው አካል ዝም ሊለው እንደማይገባም ጠይቀዋል፡፡

የሰብዓዊ ድጋፍ ከማድረግ አንጻርም ትልቅ ትኩረት እንደሚሹ እና በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ተፈናቃዮቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበሀገር መከላከያ ሠራዊት ደቡብ ዕዝ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ማልበስ መርሃ- ግብር እየተካሄደ ነው።
Next articleየታዳጊው ወጣት ሰናይ ተግባር – በደባርቅ