
ባሕር ዳር: የካቲት 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት ደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እና የቆይታ ግዜያቸውን ላጠናቀቁ የሠራዊት አባላት የሜዳሊያ የማዕረግ ማልበስ እና ሽልማት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።
የማዕረግ አሰጣጡ ሥነ-ስርዓት በመከላከያ ሠራዊት የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ኢተፋ ራጋን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በተገኙበት እየተከናወነ ነው።
የማዕረግ እድገቱ እየተሰጠ ያለው የዕዙ የላቀ የግዳጅ እፈፃፀም ላስመዘገቡ እና የቆይታ ግዜያቸውን ላጠናቀቁ የሠራዊት አባላት እንደሆነ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
የማዕረግ ዕድገቱ የባለ ሌላ ማዕረግ፥ መስመራዊ መኮንን እና ከፍተኛ መኮንን እንደሚያካትት ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።
የማዕረግ አሰጣጡ ሥነ-ስርዓቱ ለ33 የዕዙ አባላት ከምክትል አስር አለቃ እስከ ሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ የማልበስ ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/