
ጎንደር: የካቲት 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ራሱን በሐሰት እንደታገተ አድርጎ የደበቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን በጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ1ኛ ፓሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የጽሕፈት ቤቱ ተወካይ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስማቸው ፈንታ የተጠርጣሪ ግለሰቡ ባለቤት የካቲት 02/2014 ዓ.ም ባመለከቱት መሰረት ፖሊስ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል። ታገትኩ ያለው ግለሰብ ጎንደር ከተማ አርባባ አካባቢ እንደተጋተ መረጃ ሰጥቶ እንደነበርም ተናግረዋል።
ታገትኩ ያለው ግለሰብ በሰጠው መረጃ እና በተደረገው ክትትል ጥርጣሬ የገባው ፖሊስ ከቴሌ ጋር ተቀናጅቶ በሠራው ሥራ ተጠርጣሪው ደባርቅ ከተማ ሆቴል ቤት አልጋ ይዞ በቁጥጥር ስር መዋሉን ምክትል ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።
ተጠርጣሪው በማጭበርበር ወንጀል ያልተገባ ሀብት ለማካባት ፈልጎ ያደረገው ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳለ የገለፁት ምክትል ኢንስፔክተር ስማቸው የወንጀሉን አፈፃፀም ከፖሊስ መምሪያ ጋር በተፈጠረ ቅንጅት ግብረኃይል ተቋቁሞ የማጣራት ሥራ እየተከናወነ መኾኑንም ተናግረዋል።
ኅብረተሰቡ በመሰል ወንጀል የማጭበርበር ድርጊቶች እንዳይታለል ምክትል ኢንስፔክተሩ አሳስበዋል።
ዘጋቢ:- ፍፁምያለምብርሃን ገብሩ – ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/