
የካቲት 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አፍሪ-ኤግዚም ባንክ የአፍሪካን የንግድ ትስስር ለማሳደግ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ በእጥፍ የሚያሳድግ መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት ገለጹ።
የአፍሪ-ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ቤኔዲክት ኦርማህ ለኢዜአ እንደገለጹት ባንኩ የገንዘብ አቅሙን በማሳደግ የአህጉሪቷን የንግድ ትስስር ለማጎልበት በልዩ ትኩረት ይሠራል።
የአፍሪካ ሕብረት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ባንኩ ዓመታዊ የገንዘብ ምጣኔውን ወደ 6 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር እንዲያድግ መደረጉን ገልጸዋል።
የአህጉሪቷን የንግድ እንቅስቃሴ ለመደገፍ በሚያስችል መልኩ ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ለተለያዩ ሀገራት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
የአፍሪካን ወጪና ገቢ ንግድ ለመደገፍ የተቋቋመ ባንክ በመሆኾኑ የሀገሮችን የንግድ እንቅስቃሴ በገንዘብ የመደገፍና የማበረታታት ኃላፊነት አለበት ብለዋል።
የአህጉሪቱን እድገት ለማሳለጥ የንግድና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ የብድር፣ የመድህንና ሌሎች የፋይናንስ ድጋፎችን ያደርጋል ነው ያሉት።
የኢንፖርት ኤክስፖርት ባንክ የኾነው አፍሪ-ኤግዚም ባንክ ለአፍሪካዊያን ተጠቃሚነት በአፍሪካ መንግሥታት የተቋቋመ በመሆኑ ሌሎች መደበኛ ባንኮች ማከናወን የማይችሉትን ክፍተት እየሞላ መሆኑን ፕሮፌሰር ቤኔዲክት አብራርተዋል።
አፍሪ-ኤግዚም ባንክ ባለፉት አምስት ዓመታት የአፍሪካን የንግድ እንቅስቃሴ ለመደገፍ 20 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ፈሰስ ማድረጉን አስታውሰዋል።
በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ደግሞ በእጥፍ የማሳደግ እቅድ መያዙን ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።
የኢንፖርት ኤክስፖርት ባንክ የኾነው አፍሪ-ኤግዚም ባንክ እ.ኤ.አ. በ1993 በአፍሪካ ልማት ባንክ ስር የተፈጠረ የፓን አፍሪካ ባለብዙ ወገን የንግድ ፋይናንስ ተቋም ነው።
አፍሪ-ኤግዚም ባንክ በኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ የሥራ እድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እየደገፈ ይገኛል።
በቅርቡም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር 1 ቢሊየን ዶላር ብድር ማግኘት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/