
ወልድያ: የካቲት 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የማኅበራዊና ልማት ኮሚሽን እና ኮርድ ኤድ በጋራ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ከ2 ሺህ በላይ ወገኖች የምግብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
በተደረገላቸው ድጋፍ ምሥጋና ያቀረቡት ተጎጅዎቹ በቀጣይ ወደ መደበኛ ኑሯቸው ለመመለስ ጠንክረው እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የባሕር ዳር ደሴ ሀገረስብከት ኮምቦልቻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አባ ዮሐንስ ወሰንና የኮርድ ኤድ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ መርኃግብር ኃላፊ አቶ አሕመድ ሙሐመድ ለተጎጅዎቹ ድጋፍ የሚውል ከ6 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል። ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ረጅ ድርጅቶቹ ለተጎጅዎቹ ጊዜያዊ ድጋፍ ከማድረግ በዘለለ ኑሯቸው በዘላቂነት የሚቀየርበትን ፕሮጀክት ቀርጸው ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- በቀለ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/