
የካቲት 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአውራምባ ማኅበረሰብ 50ኛ አመት በዓል “ኑ ጠቃሚ እሴቶቻችንን በጋራ እንገንባ” በሚል ሐሳብ በማክበር ላይ ይገኛል። በበዓሉ ላይ የተገኙት የማኅበረሰቡ መስራች ክቡር ዶክተር ዙምራ ጠብን ከማብዛት ፍቅርን እየዘሩ መኖር ያስፈልጋል ብለዋል። እንደ ክቡር ዶክተር ዙምራ ገለፃ፤ የሰው ልጆችን ጉዳት በመረዳት መኖር ያስፈልጋል፤ የወገኑን ችግር የማይረዳ ሰው ከእንስሳት ተለይቶ ሊታሰብ አይገባውም።
የክብር ዶክተር ዙምራ ባለቤት ወይዘሮ እናነይ ክብረት መጥፎ አመለካከትን በማስተካከል ለቀጣይ ትውልድ በጎነትን ማውረስ ይገባል ብለዋል። ወይዘሮ እናነይ የማኅበረሰቡን መልካም እሴት ለማስቀጠል እሳቸውና ባለቤታቸው የሚበሉትን እስኪያጡ የደረሱበት ወቅት እንደነበርም አስታውሰዋል።
ኢፕድ እንደዘገበው የአውራምባ ማኅበረሰብ እምነቱ ሥራ መለያው አንድነት ኾኖ ለ50 ዓመታት በስኬት ማሳለፉን በመድረኩ ተገልጿል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን
በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/