በኢትዮጵያ ለሚገኙ የውጭ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በወቅታዊ ሀገራዊ ኹኔታ ገለጻ ተደረገ።

115

አዲስ አበባ፡ የካቲት 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገራት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ፍስሃ ሻውል ባደረጉት ገለጻ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነትና በህዳሴ ግድቡ በአንዳንድ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጫና ተደርጓል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርነት እንዳይከስት ነገሮችን በትዕግስት ሲያስኬድ እንደነበር ጠቅሰዋል። በህዳሴ ግድቡ ዙሪያም የሦስትዮሽ ውይይት ጋር ማድረጉን ጠቁመዋል።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕጎችን አክብራ ብዙ ርቀት ብትሄድም አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን ከማድረግ አልፎ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ወረራ አድርጓል ብለዋል።

አሸባሪው ቡድን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት ጦርነት መክፈቱን አብራርተዋል፡፡ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት ለሽንፈት መዳረጉን ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ችግሮችን ለመቅረፍ ብዙ ጥረት አድርጎ እንደነበረ ያስታወሱት ብርጋዴር ጀነራሉ አሸባሪው ቡድን በራሱ ተነሳሽነት ወደ ጦርነት በመግባቱ መንግሥት ከሕዝብን አንድ በመኾን የሽብር ቡድኑን ሊደመስሰው እንደቻለ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር መሥራት ለሚፈልጉ ኹሉ ተባባሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በተቸገረችበት ወቅት ድጋፍ ላደረጉ ኹሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አብነት እስከዚያ -ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝የተፈናቀሉ ወገኖችን ጊዜያዊ ችግር ለማቃለል በክልሉና በአጋር አካላት ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ጥረት እየተደረገ ነው❞ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም
Next articleየአውራምባ ማኅበረሰብ 50ኛ ዓመት በዓል እየተከበረ ነው።