❝የተፈናቀሉ ወገኖችን ጊዜያዊ ችግር ለማቃለል በክልሉና በአጋር አካላት ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ጥረት እየተደረገ ነው❞ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም

215

ሰቆጣ: የካቲት 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ብቻ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ተፈናቅለው በጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ የተጠለሉ ወገኖች ቁጥራቸው ከ35 ሺህ እንደሚበልጥ ተነግሯል።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የጋዜጠኞች ቡድን በሰቆጣ ከተማ የተፈናቀሉ ወገኖች መጠለያ ተገኝቶ እንደታዘበው በርካቶች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። በተጨማሪም የጊዜያዊ መጠለያ እጥረት ለችግር እንደዳረጋቸውም ተፈናቃዮቹ አስረድተዋል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም “የተፈናቀሉ ወገኖች ጊዜያዊ ችግር ለማቃለል በክልሉና በአጋር አካላት ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ጥረት እየተደረገ ነው” ብለዋል።

ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችም የዱቄት፣ አልባሳት እና ፍራሽ ድጋፍ እየቀረበ እንደሚገኝም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። የጊዜያዊ መጠለያ እጥረትን ለመቅረፍም ታቅዶ እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- እያያው ተስፋሁን – ከሰቆጣ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝ግብፅና ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መደገፍ አለባቸው❞ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
Next articleበኢትዮጵያ ለሚገኙ የውጭ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በወቅታዊ ሀገራዊ ኹኔታ ገለጻ ተደረገ።