
ባሕር ዳር: የካቲት 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እንዳስታወቀው በጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን ዲማ ወረዳ ኡኩቡ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የካቲት 2/ 2014 ዓ.ም ከለሊቱ በ5 ሰዓት ከደቡብ ሱዳን አጎራባች አካባቢ ሰርገው የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች አምስት ህጻናትን አግተው ወሰደዋል።
እነዚሁ ታጣቂዎች በስደተኞች ጣቢያው በከፈቱት ተኩስም ሁለት ሴቶችን አቁስለዋል።
በተመሳሳይ በቀጣዩ ቀን ማለትም የካቲት 3/ 2014 ዓ.ም ዳግም ታጣቂዎቹ በጎግ ወረዳ በከፈቱት ጥቃት የአንድ ግለሰብ ህይወት ማለፉን አገልግሎቱ ገልጿል።
በስፍራው የተፈጠረውን ክስተት ለማጣራትና ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ እንዲሁም የታገቱ ህጻናትንም ለማስመለስ የፌዴራል ፖሊስ ከክልሉ የጸጥታ ኀይል ጋር በመሆን በጋራ እየሰራ ይገኛል።
ከዚህ በፊት የጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች ከአጎራባቹ የሙርሌ ጎሳ ሰርገው በሚገቡ ታጣቂዎች ተመሳሳይ የህጻናት እገታና ጥቃት መፈጸሙን አስታውሷል።
የአካባቢውን ጸጥታ ለማስጠበቅ የሁለቱ ሀገራት አጎራባች ክልሎች አስተዳደርና የፌዴራል ፖሊስ ችግሮችን ለመፍታት ባደረጉት ጥረት በአካባቢው በታጣቂዎች ይፈጸሙ የነበሩ የሰረጎ ገብ ታጣቂዎችን እንቅስቃሴ ለመቀነስ ተችሎ እንደነበር አስታውቋል።
አሁን የተፈጠረውን ክስተት በተመለከተም የታገቱትን አምስት ህጻናት ለማስመለስ ከሚደረገው ጥረት ባሻገር በሁለቱም ሀገራት አጎራባች አካባቢዎች የሚኖሩ የሀገር ሸማግሌዎችንና የማኅበረሰቦቹን ተወካዩች ባሳተፈ መልኩ ዘላቂ ሰላምን በአካባቢው የማስፈን ጥረት ይቀጥላል ብሏል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/