“አማራ የሚገጥመውን የኅልውና ስጋት ለመሻገር አንድ ሆኖ መደራጀት አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው” ዓለምአቀፍ የሕግ ምሁሩ ዶክተር ዘላለም ሞገስ

204

አዲስ አበባ: የካቲት 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአንድ ሀገር ውስጥ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሲከሰት ለሌሎች ተጓዳኝ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መፈጠር መንስኤ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ አሸባሪዉ ትህነግ ከስልጣን ከተወገደ ማግስት ጀምሮ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በቀዉስ ማዕበል ዉስጥ እየዋኘ ይገኛል።
ይህ ደግሞ ሀገሪቱን ከፖለቲካዉ ባሻገር ለኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ አለመረጋጋቶች ዳርጓታል፡፡
ፖለቲካዊ አለመረጋጋቱን ተከትሎ ለከፍተኛ ችግር ከተጋለጡት የሀገሪቱ አካባቢዎችም የአማራ ክልል አንዱ ነዉ፡፡
አማራ የገጠመውን የኅልዉና ስጋት እንዲሻገር አንድ ሆኖ መደራጀት አማራጭ የሌለዉ መፍትሔ መሆኑን ወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ እንደሚያሳይም የዓለምአቀፍ ሕግ ምሁሩ ዶክተር ዘላለም ሞገስ አስገንዝበዋል።
በክልሉ ተደጋጋሚ የሆነ የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መለዋወጥ ለአስተዳደራዊ አገልግሎት ምቹ አለመሆን የጠቀሱት ምሁሩ ይህም በጥንቃቄ ሊመረመር ይገባል ብለዋል፡፡
የአማራ ሕዝብን የሚወክሉ የመንግሥት ኀላፊዎች፣ ሊሂቃን እና ሕዝቡ ሁሉም እንደየሚናቸዉ የድርሻዉን መወጣት እና ተናቦ መስራት ወቅቱ የሚጠይቀዉ አስገዳጅ ሁኔታ መሆን እንዳለበትም ምክረ ሐሳባቸውን አስቀምጠዋል፡፡
ዘጋቢ:–በለጠ ታረቀኝ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleጣይቱ ብጡል (ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ)
Next articleበጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ከደቡብ ሱዳን አጎራባች አካባቢ ሰርገው የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች አምስት ህጻናትን አግተው መውሰዳቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።