
የካቲት 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የ”በቃ” ዓለምአቀፍ ንቅናቄን በማስተባበር በሰሜን አሜሪካ ከሚንቀሳቀሰው “የሰላምና አንድነት ግብረኃይል” የሥራ ኃላፊዎች እና አባላትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይቱ ላይ የውጪ ኃይሎች ሀገር ውስጥ ካሉ የጥፋት ቡድኖች ጋር ጥምረት በመፍጠር ኢትዮጵያን ለማፍረስ በተለያዩ ግንባሮች የከፋ ጥፋት በመፈፀም እና የከረረ ጫና በመፍጠር የሀገርን ልዓላዊነትን ሲፈታተኑ እንደነበር አቶ ደመቀ አስታውሰዋል።
በተለይ በውጪ ኃይሎች የሚወሰዱት ፍትሐዊነት የጎደላቸው እርምጃዎች የሀገሪቱን ልዓላዊነት በእጅጉ እንደተፈታተኑ በመጥቀስ፤ ውጫዊ ጫናዎችን የመመከት ተልዕኮ ራሱን የቻለ ፈታኝ ግንባር እንደነበር አቶ ደመቀ ተናግረዋል።
እንደ አቶ ደመቀ ገለፃ ውጫዊ ጫናዎች በሚመከቱበት ግንባር በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በ”በቃ” የንቅናቄ መርህ በዓለም አደባባይ ለሀገራቸው ፍትሕን በመሻት ድምፃቸውን በስፋት አስተጋብተዋል።
በተመሳሳይ በሰሜን አሜሪካ የ”በቃ” ንቅናቄን በማስተባበር እና በመምራት “የሰላምና አንድነት ግብረኃይል” የሥራ ኃላፊዎች እና አባላት የዚህ ታሪካዊ ዘመቻ አካል በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ አቶ ደመቀ አመስግነዋል።
በኹሉም ግንባሮች ኢትዮጵያዊ አንድነት ጠብቆ እና አጥብቆ መጓዝ ተደማጭነትን ከማረጋገጡ ባሻገር ትርጉም አዘል ድሎችን ለማስመዝገብ እንደሚያግዝ ከዓለምአቀፍ ንቅናቄው ቋሚ ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል ነው ያሉት።
በሀገር አቀፍ ደረጃ መንግሥት ዘላቂ ሰላም እና ዕድገት ለማረጋገጥ ተስፋ ሰጪ እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመሩን አቶ ደመቀ በዝርዝር አብራርተዋል።
በሀገሪቱ ላይ የሚደርሱ ውጫዊ ጫናዎችን በአንድነት ከመመከት ባሻገር በብሔራዊ ደረጃ የተጀመረውን ዘላቂ ሰላም እና ዕድገት የማረጋገጥ ጥረት በሕብረት መደገፍ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/