
የካቲት 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ግሎባል አሊያንስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ10 ሚሊዮን ብር ወጪ በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ሊያካሄድ መኾኑ ተገለጸ።
ድርጅቱ በሎጊያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የማስፋፊያ ግንባታ ለመጀመር ትናንት የመሠረተ ድንጋይ ዛሬ አስቀምጧል።
እስከ 7ኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምረው የሎጊያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ወይዘሮ ህይወት ሽመልስ በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ ትምህርት ቤቱ በአንድ ክፍል እስከ 120 ተማሪዎች በተጨናነቀ ሁኔታ እያስተማረ ይገኛል።
ትምህርት ቤቱ የመማሪያና አስተዳደር ክፍሎች ጥበት በተጨማሪ የውኃና የመጸዳጀ ቤት ችግሮች ያሉበት መኾኑን ጠቁመው፤ ይህ ችግር ተማሪ የመቀበል አቅሙን እንደገደበበት ገልጸዋል።
ትምህርት ቤቱ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ ትውልድ ለመቅረጽ የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ ነው ያለው የግሎባል አሊያንስ ቦርድ ሰብሳቢ አርቲስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ፤ የትምህርት ቤቱን ችግሮች ለመፍታት የድርጅቱን አባላት በማስተባበር በቀጣይ ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግሯል።
ግንባታው እስከ 10 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚፈጅና ሥራው በአፋር ልማት ማኅበር በኩል የሚከናወን መኾኑን ጠቅሷል።
የአፋር ክልል ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ዘመን የማይሽረው ታማኝነት በተግባር አስተምሮናል ሲል አርቲስት ታማኝ ገልጿል።
“በውጭ የምትኖሩ ወንድሞቼና እህቶቼ ወገናችሁ ለሀገሩ እየከፈለ ያለውን መስዋእትነት በመረዳት በምንችለው ኹሉ ከአፋር ሕዝብ ጎን ልንቆም ይገባል” ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።
የአፋር ልማት ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኑረዲን ሰዲቅ በበኩላቸው “ግሎባል አሊያንስና አርቲስት ታማኝ በየነ ከአፋር ሕዝብ ጎን በመቆም እያደረገ ያለው ኹሉን አቀፍ ድጋፍ የሚደነቅ ነው” ብለዋል፡፡
እንደ ኢዜአ ዘገባ ግብረሰናይ ድርጅቱ የገንዘብ ድጋፍ የሚገነባው የትምህርት ቤት የማስፋፊያ 8 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ባለሁለት ብሎክና የአስተዳደር ሕንጻን ጨምሮ ሌሎች ግንባታዎችን ያካተተ መሆኑን ጠቅሰው፤ ግንባታው በ8 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/