ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለኢፌዴሪ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ምስጋና አቀረቡ።

268

ባሕር ዳር: የካቲት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለኢፌዴሪ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አመራሮች እና አባላት ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወዳጅነት አደባባይ በተዘጋጀው መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር “የኢትዮጵያ የፀጥታ አካላት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ኩራት መሆናችሁን በተግባር ስላረጋገጠችሁ ብዙ የአፍሪካ መሪዎች ኮርተውባችኋል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት፣ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ለኦሮሚያ ፖሊስ፣ ለሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል እና ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምስጋና ማቅረባቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ባለፉት ወራት የተካሔዱት ታላላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶች የኢትዮጵያን ገጽታ ለዓለም በሚያጎላ መልኩ በሰላም እንዲጠናቀቁ የፀጥታ አካላቱ ተቀናጅተው በመስራት ሰላም ስላረጋገጡ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና ያቀረቡላቸው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ጎልተው የሚታወሱ ታሪኮቿ።
Next articleግሎባል አሊያንስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ10 ሚሊዮን ብር ወጪ በሎጊያ ከተማ የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ሊያካሂድ ነው፡፡