በአሜሪካ ኦሪገን የአማራ ማሕበር በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ760 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡

92

ባሕር ዳር: የካቲት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ ኦሪገን ስቴት የአማራ ማሕበር ሊቀመንበር ዘላለም ስንሻው እንዳሉት ድጋፉ በአሜሪካ ኦሪገን ስቴት ከሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እና ደጋፊዎች የተሰበሰበ ነው፡፡ ማሕበሩ ያደረገው ድጋፍ የመጀመሪያ አለመኾኑን ያነሱት አቶ ዘላለም ከዚህ በፊትም በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ አካባቢ በተከሰተው ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡ ከሌሎች ሲቪክ ማሕበራት እና የሃይማኖት ተቋማት ጋር በመተባበርም በጦርነቱ ለተጎዱት የአማራና አፋር ክልሎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም በውጭ የሚኖሩ ዲያስፖራዎች በገንዘበ፣ በሙያ፣ በዲፕሎማሲው ሥራ አምባሳደር ኾነው ሀገራቸውን እንደሚያግዙ አንስተዋል፡፡ ይሕ እንዲሳካም መንግስት ከዲያስፖራው ጋር ችግሮችን በመለየት መስራት እንደሚገባው ጠቅሰዋል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እታገኝ አደመ በዲያስፖራው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ኮሚሽኑም ድጋፉን በፍትሐዊነት ችግሩ ባለባቸው አካባቢዎች እንደሚያሰራጭ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት 11 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሕዝብ የእለት ምግብ ድጋፍ እየተደረገ መኾኑን ወይዘሮ እታገኝ አንስተዋል፡፡

መንግሥት ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ልዩ ልዩ ድርጅቶች የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ እያደረጉ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአሸባሪው የትህነግ ቡድን በሱዳን ድንበር ከሌሎች ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር ያደረገውን እንቅስቃሴ ማምከን መቻሉን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ገለፁ።
Next articleየጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ጎልተው የሚታወሱ ታሪኮቿ።