አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሱዳን ድንበር ከሌሎች ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር ያደረገውን እንቅስቃሴ ማምከን መቻሉን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ገለፁ።

215

የካቲት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሱዳን ድንበር ከሌሎች ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር ያደረገውን እንቅስቃሴ ማምከን መቻሉን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ገልጸዋል።
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥና የዓድዋ ድል ጀግና ሜዳይ ተሸላሚው ጄነራል ጌታቸው ጉዲና፣ የሽብር ቡድኑ በግንባር እያደረገ ያለውን ጥቃት ለማፋጠን በሱዳን ድንበር ከሌሎች ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ያደረገው ትስስር የምዕራብና የማዕከላዊ ጎንደር ብሎም የወልቃይት አካባቢ መሥተዳድርና የፀጥታ ኃይሎች ከሠራዊቱ ጋር ጥምረት በመፍጠር ባደረጉት ወደር የሌለው ተጋድሎ ማምከን መቻሉን ገልጸዋል። ለአካባቢው አመራርና ሕዝብም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የሽብር ቡድኑ በሕይወት እስካለ ድረስ ከጥፋት የማይመለስና ለእኩይ ድርጊት የተፈጠረ በመኾኑ ላይመለስ እስከወዲያኛው ማሰናበት እንደሚገባ ተናግረዋል።
እስካሁን የተሠሩ ሥራዎች በውጤታማነት የተቋጩት ጠንካራ የትብብርና የመደጋገፍ ባሕል በመስፈኑ እንደሆነ ነው የገለፁት ጄነራሉ። ከድል ማግስትም ትብብርን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleፍርድ ቤቱ በሰኔ 15ቱ ጥቃት ተጠርጣሪዎች ላይ ብይን ሰጠ፡፡
Next articleበአሜሪካ ኦሪገን የአማራ ማሕበር በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ760 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡