ፍርድ ቤቱ በሰኔ 15ቱ ጥቃት ተጠርጣሪዎች ላይ ብይን ሰጠ፡፡

848

ባሕር ዳር: የካቲት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሰኔ 15/2011 ዓ.ም በክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች እና የጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር ያሉ ተከሳሾች የፍርድ ሂደታቸው ሲታይ ቆይቷል፡፡

እስካሁን በነበረው የፍርድ ሂደት 20 ተጠርጣሪዎች በነጻ ሲለቀቁ ሦስት ተጠርጣሪዎች ደግሞ በሌሉበት ጥፋተኛ ተብለው ነበር፡፡ በዛሬው የችሎት ውሎም በ32 ተጠርጣሪዎች ላይ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡

በፍርድ ሂደቱ ዐቃቤ ሕግ 76 የሰው፣ የሰነድ፣ የድምጽ እና ምስል ምስክሮች መቅረባቸውን ያወሳው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾችም የመከላከያ ምስክሮችን እና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርበው ሲከራከሩ መቆየቱን ነው የገለጸው፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው የችሎት ውሎም በ32 ተከሳሾች ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡ በክስ መዝገቡ ከቀረቡት ተከሳሾች መካከል አራት ተከሳሾችን በነጻ አሰናብቶ በ28ቱ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ የተከራካሪ ወገኖችን የጥፋት አስተያየት ለመቀበልም ለየካቲት 07/2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአሸባሪዎቹን ትህነግ እና ሸኔ በጋራ ለመዋጋት እንደሚሠሩ የአማራና የኦሮሚያ ክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች አስታወቁ።
Next articleአሸባሪው የትህነግ ቡድን በሱዳን ድንበር ከሌሎች ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር ያደረገውን እንቅስቃሴ ማምከን መቻሉን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ገለፁ።