አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር አሊ አልሳዲቅ ጋር በኹለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ፡፡

222

የካቲት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር አሊ አል ሳዲቅ ጋር በኹለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
አምባሳደር ይበልጣል በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ያለውን ለዘመናት የዘለቀ ኹለንተናዊ የኹለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ልዩነት የሚታይባቸውን የድንበር እና የሕዳሴ ግድብ ጉዳዮች ለመፍታት ተቀራርቦ መሥራት ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።
መተማ-ገለባት የድንበር ኬላ ለዜጎች እንቅስቃሴ ክፍት እንዲደረግ፣ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን በኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተጣለው የመውጫ ክፍያ እንዲሰረዝ ወይም የኢትዮጵያውያኑን ኑሮና ገቢ ኹኔታ ያማከለ እንዲሆን ጥያቄ አቅርበዋል።
የሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር አሊ አልሳዲቅ በበኩላቸው በኹለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ በመጥቀስ የመተማ-ገለባት ድንበር እንዲከፈትና የመውጫ ቪዛ ጉዳይ እልባት ያገኙ ዘንድ እንደሚሠሩበት ገልፀዋል።
በሀገራቱ መካካል ያለውን ግንኙት ካለበት ደረጃ ለማሻሻል የሚስተዋሉ ጅምር እንቅስቃሴዎችን ለማስቀጠል፣ በድንበር እና በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ እንዲሁም በሌሎች ስትራቴጂክ ጉዳዮች ዙሪያ ተቀራርቦ ለመነጋገርና የጋራ መፍትሔዎችን ለማበጀት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ከመግባባት ላይ መደረሱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleʺለአማራ ሕዝብ የምናስብ፣ የምንቆረቆር፣ የአማራ ሕዝብ ሕመም የሚያመን ከሆነና የአማራን ጥንተ ተጋድሎ የምናውቅ ከሆነ በአንድነት መቆም አለብን” ዶክተር ዘመነወርቅ ዮሐንስ
Next articleአሸባሪዎቹን ትህነግ እና ሸኔ በጋራ ለመዋጋት እንደሚሠሩ የአማራና የኦሮሚያ ክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች አስታወቁ።