የኦሮሚያ ክልል ለአማራ ክልል የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

650

ባሕር ዳር: የካቲት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኦሮሚያ ክልል በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ባሕር ዳር መግባታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ርእሰ መሥተዳድሩ በአማራ ክልል በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለአማራ ክልል አስረክበዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ትልቅ ፈተና ውስጥ ነው ያለችውም ብለዋል። ብዙ መፈናቀልና የሰው ሕይወት መጥፋት የነበረበት ነው ብለዋል። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጥቃት የከፈተበት፣ በኦሮሚያ ክልል ያሉ ተላላኪዎችም ጥፋት የፈፀሙበት ነው ብለዋል። በከፍተኛ መስዋእትነት ሀገር ቀጥላለች ነው ያሉት።
የተከፈለው ዋጋ ለሀገር የኾነ ቢሆንም ጠባሳው ከባድ መሆኑን አንስተዋል። ከዚህ በላይ ድጋፍ ማድረግ ይገባ ነበር ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ከአማራ ክልል ጎን መቆማችንን ለማሳየት ድጋፍ አድርገናል ነው ያሉት።
❝በኦሮሚያ ክልል የአሸባሪው ሸኔ ጥቃት እና ድርቅ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶብናል፤ ፈተና ውስጥ ነን፤ ነገር ግን ካለን ለማካፈል መጥተናልም❞ ብለዋል። የአማራ ክልል በሚጠይቃቸው ኹሉ ለማገዝና ክልሉን ከነበረበት ከፍ አድርጎ ለመገንባት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ፈተናዎችን ለማለፍ አንድነት ያስፈልገናል፤ ከአንድነት ውጭ ያለው መንገድ የውድቀት ነው ሲሉም ገልፀዋል። ከተጋገዝን እና በአንድነት ከቆምን ፈተናው ከፍ ያደርገናል ነው ያሉት።

ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በአሸባሪው ትግራይ ወራሪ ኃይል በደረሰብን ጉዳት አይዟችሁ ለማለት በመምጣታቸሁ እና ድጋፍ በማድረጋቸሁ እናመሰግናለን ብለዋል። ወያኔ የኢትዮጵያውያን ጠላት መሆኑን ያነሱት ዶክተር ይልቃል አፋርና አማራ ሲጠቃ የኦሮሚያ ክልል አብሮ መቆሙን ነው ያስታወሱት።
ኢትዮጵያውያን አንድ ኾነን በሄድን ጊዜ ጠላታችን እናሸንፋለን ነው ያሉት። በአንድነት ጠላታችን አሸንፈናልም ብለዋል። ድሉንም ዘላቂ ለማድረግ ብዙ ርቀት መሄድ ይኖርብናል፤ ለዚህ ደግሞ ሳንዘናጋ መታገል ይገባናል ነው ያሉት።
የደረሰው ጥቃት ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል። ዜጎች መገደላቸውን፣ ሴቶች መደፈራቸውን ገልፀዋል። መላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ማድረጋቸውንም አመላክተዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን አሁንም ለዳግም ወረራ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ይልቃል ጠላትን የሚመክት ዝግጅት ማድረግ ይገባልም ብለዋል።
አሸባሪው ሸኔና ሌሎች ተላላኪ ቡድኖችን መታገል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በአንድነት መቆም ከተቻለ ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ እናቆማለንም ብለዋል።
ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Amajjii 30/2014
Next articleʺለአማራ ሕዝብ የምናስብ፣ የምንቆረቆር፣ የአማራ ሕዝብ ሕመም የሚያመን ከሆነና የአማራን ጥንተ ተጋድሎ የምናውቅ ከሆነ በአንድነት መቆም አለብን” ዶክተር ዘመነወርቅ ዮሐንስ