
ባሕር ዳር: የካቲት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተደድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን በዛሬው ዕለት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድሩ ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ በሁለቱም ክልል ሕዝቦች ሕገ-መንግሥቱን መሠረት በማድረግ የሕዝብ ለህዝብ ግንኘነት በማጠናከር የተጀመሩ የውይይት መድረኮችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።
የሁለቱንም ክልል ሕዝቦች የጋራ የሠላምና ልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጋራ ዕቅድ በማወጣት የፖለቲካና የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ከመሥራት ጎን ለጎን የሰላምና የጸጥታ ሥራዎችን አጠናክሮ በመስራት ለህዝቦች የሠላምና የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ነው የገለፁት።
አቶ አሻዲሊ ሀሠን በበኩላቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ክልል ሕዝቦች የጋራ የሰላምና የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በባለፋት ጊዚያት ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች ሲስሩ ቆይተዋል ብለዋል፡፡
በቀጣይም የሁለቱን ክልልች ሕዝቦች ለዘመናት የቆየውን ወንድማማችነትና አብሮነት ይበልጥ ትስስሩን በማጠናከር የጋራ ሰላምና የልማት ጠቃሚነትን ለማጎልበት እንደሚሰራም ገልጸዋል።
ርእሰ መስተዳድሩ አያይዘውም በክልሉ በመተከል ዞን የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት እና በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የጸጥታ ኃይሎች በቅንጅት እየከፈሉት ላለው መስዋእትነት የላቀ ምስጋና አቅርበው እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል የገጠሙንን ፈተናዎች ተቀራርቦ በመስራት ችግሮችን በአሸናፊነት ልንወጣ ይገባል ማለታቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/