
የካቲት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
በአሜሪካ ዴንቨር ከተማ ነዋሪ ፍጹም ፍቃዱ አስተባባሪነት የተሰበሰበ ከ500 ሽህ ብር በላይ የቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል፡፡
ወይዘሮ አረጉ ፈንታው በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ መሐል አምባ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በፈጸመው ግፍ ባለቤታቸውን አጥተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ኹለት ልጆቻቸውን እያሳደጉ ቢኾንም የሸብር ቡድኑ ባደረሰው ጥፋት ሕይወት አስቸጋሪ እንደኾነባቸው ተነግረዋል፡፡ ሌላዋ ነዋሪ ወይዘሮ ሀድያ አሊ የሸብር ቡድኑ በከባድ መሳሪያ በመኖሪያ ቤታቸው ጉዳት ደርሶባቸው ከሞት ቢተርፉም በደረሰው ጉዳት ሕይወታቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በሀብሩ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌ ለሚኖሩ ተጎጂዎች በአሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር ከተማ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን ያስተባበሩትና ያስረከቡት አቶ አራጋው ሞላልኝ ተጎጂዎች ባሉበት አካባቢ በመንቀሳቀስ ድጋፍ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከምንጊዜውም በላይ ለተጎጂዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ አቶ አራጋው ገልጸዋል፡፡
የመሐል አምባ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ሞላ ገበየ ድጋፍ ላበረከቱላቸው በአሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር ከተማ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ:- ደጀን አምባቸው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/