
የካቲት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሳይንስ እና ትምህርት ዘርፍ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ትብብር እና የሕግ ማዕቀፎችን ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከሀገሪቱ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ጋር ተወያይተዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በሳይንስ እና ትምህርት ዘርፍ እያካሄደች ያለውን የማሻሻያ እቅዶች በተመለከተ ለአምባሳደሩ አብራርተውላቸዋል።
ሩሲያ በርካታ ኢትዮጵያውያንን በተለያዩ ዘርፎች በማሰልጠን ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎችን ስታበረክት የቆየች መኾኑን ያወሱት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ይህም ሩሲያ በኢትዮጵያ የሰለጠነ የሰው ኃይል እንዲኖር ያደረገችው አስተዋጽኦ ዘመን ተሻጋሪ ነው ብለዋል።
የኹለቱ ሀገራት እውነተኛ የወዳጅነት ምልክት የኾነው የቀድሞው የባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩት የአኹኑ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያ ካሉ አንጋፋ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ የኾነው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በርካታ ልሂቃንን እንዳፈራ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል።
በቀጣይም ኹለቱ ሀገራት ግንኙነታቸውን በማሳደግ የተሻለ ለመሥራት የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
በታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/