
የካቲት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ደርሶባቸው በዱብቲ ሆስፒታል የህክምና ዕርዳታ የሚደረግላቸውን ሕጻናትን ጠየቁ።
ሕጻናቱ ጉዳት የደረሰባቸው የሽብር ቡድኑ በተኮሰው ከባድ መሳሪያ መኾኑ ተገልጿል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትና የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ በተጨማሪም በሠመራ ከተማ የሚገኘውን የዓለም ምግብ ድርጅት መጠባበቂያ መጋዘንን የምግብ ክምችት ተመልክተዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ፣ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/