
የካቲት 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የሚጀምር መኾኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አበበ ግርማ ገለጹ።
በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ውድመትና ዘረፋ የተፈፀመበት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የመልሶ ጥገና ሥራ በማከናወን ከየካቲት 07/2014 ዓ.ም ጀምሮ የማታ ተማሪዎችን ተቀብሎ ዳግም የመማር ማስተማር ሥራውን ይጀምራል።
የመጀመሪያ ዓመትና ተመራቂ ተማሪዎችን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በመቀበል ለማስተማር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አበበ ግርማ ለኢዜአ ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሃብት ዘረፋና ውድመት የደረሰበት መኾኑን አስታውሰው የተለያዩ ጥረቶች ተደርገው ለዳግም የመማር ማስተማር ሂደት ዝግጁ ሆኗል ብለዋል።
ከሌሎች ዘጠኝ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ባገኘው ድጋፍ በመጀመሪያው ምዕራፍ ዳግም ሥራ ለመጀመር የሚያስችለው ደረጃ ላይ ይገኛልም ነው ያሉት።
በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ በመኾኑ ወላጆች ልጆቻቸውን ያለምንም ስጋት ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲልኩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከየካቲት 07/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የማታ ተማሪዎችን በመቀበል ሥራውን የሚጀምር ሲሆን በተከታይም የመጀመሪያ ዓመትና ተመራቂ ተማሪዎችን ይቀበላል ተብሏል።
ዩኒቨርሲቲው ለስድስት ወራት በወራሪውና አሸባሪው የትግራይ ቡድን ስር በነበረበት አጋጣሚ በቡድኑ ሙሉ ለሙሉ ንብረቶቹ መዘረፋቸውን ጠቅሰዋል።
ዩኒቨርሲቲውን ሥራ ለማስጀመር በተደረገው ርብርብ የተማሪዎች መኝታ፣ የመማሪያ ክፍሎችና ሌሎች ቁሳቁስ ለማሟላት መቻሉን ጠቁመዋል።
በቀጣይም ከመንግሥት፣ ከበጎ አድራጊዎችና ከቀድሞ ተማሪዎች ጋር በመኾን ዩኒቨርሲቲውን የማሟላት እቅድ መያዙን ተናግረዋል።
በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘረፋና ውድመት የተፈፀመባቸው የወሎ፣ የመቅደላ አምባና የወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ ተማሪዎችን በመቀበል ዳግም ሥራ የሚጀምሩ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/