የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በኅልውና ዘመቻው በጀግንነት ለተሰው ዘማች ቤተሰቦችና ጉዳት ለደረሰባቸው የጸጥታ ኃይል አባላት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

176

ገንዳ ውኃ: የካቲት 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በኅልውና ዘመቻው በተለያዩ ግንባሮች በጀግንነት ለተሰው የዘማች ቤተሰቦች እና ለተጎዱ የጸጥታ ኃይል አባላት 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ያስረከቡት የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው የተደረገው ድጋፍ በቂ ባይኾንም ጀግንነታቸውን ለማስታወስ እና ከጎናቸው መሆናችንን ለመግለጽ ነው ብለዋል።
በጀግንነት እና በክብር የተሰው ቤተሰቦችን መደገፍ፣ መንከባከብ፣ ክብር መስጠት፣ አይዟችሁ ማለትና በየትኛውም ጊዜ ከጎናቸው መቆም እንደሚገባም አቶ ደሳለኝ ገልጸዋል።
የሕዝብ አንድነትን በማጠናከር አካባቢውን የልማትና የሰላም ቀጣና ማድረግ ይገባልም ብለዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ቢክስ ወርቄ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በመደምሰስ የዞኑ ሚሊሻና ፋኖ አኩሪ ታሪክ እና ጀብድ ፈጽሟል ነው ያሉት፡፡ ለዚህም ላቅ ያለ ምሥጋና ይገባል ብለዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ቤተሰቦችና የጸጥታ ኃይል አባላትም በዞን አስተዳደሩ ለተደረገላቸው የገንዘብ ድጋፍ አመስግነዋል።
ዘጋቢ፡-ቴዎድሮስ ደሴ -ከገንዳ ውኃ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና አፍሪ-ኤግዚም ባንክ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።
Next articleየወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይጀምራል።