
የካቲት 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና አፍሪ-ኤግዚም ባንክ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረመዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የኢንፖርት ኤክስፖርት ባንክ የኾነው አፍሪ-ኤግዚም ባንክ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ነው የተፈራረሙት።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እና የአፍሪ-ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ቤኔዲክት ኦርማህ ፈርመዋል።
የንግድና ኢንቨስትመንት፣ የሥራ እድል ፈጠራና በድህነት ቅነሳ ላይ ለሚደረጉ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ስምምነቱ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ ኢትዮጵያን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር በኢንቨስትመንት ትስስር ለመፍጠር እያደረገች የሚገኘውን ጥረት ለማገዝም እንደሚረዳ ተገልጿል።
አፍሪ-ኤግዚም ባንክ እ.ኤ.አ. በ1993 በአፍሪካ ልማት ባንክ ስር የተፈጠረ የፓን አፍሪካ ባለብዙ ወገን የንግድ ፋይናንስ ተቋም ነው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/