
ጥር 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴና የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው ቀብሪ በያህ ወረዳ መረጋቾ ቀበሌ የሚገኙ ዜጎችን ጠየቁ።
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች የሚገኙበትን ኹኔታ ጠይቀዋል።
ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ እና ምክትል ዋና ጸሐፊዋ አሚና በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ የተፈናቀሉ ወገኖች የሚገኘበትን ኹኔታ የተመለከቱት በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በቀብሪ በያህ ወረዳ መረጋቾ ቀበሌ የሚገኙ ዜጎችን ነው።
እንደ ኢዜአ ዘገባ ፕሬዚዳንቷ እና ምክትል ዋና ጸሐፊዋ በድርቁ የተፈናቀሉ ወገኖች የሚገኙበትን ኹኔታ የተመለከቱት ከሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድን ጨምሮ ከሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር በመሆን ነው።
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ተጎጂዎችን አጽናንተዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/