❝ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ጉባኤን በስኬት ማጠናቀቋ የውጭ ተፅዕኖን መቋቋም እንደምትችል ያሳየችበት ነው❞ የዓለምአቀፍ ሕግ ባለሙያ ዘላለም ሞገስ (ዶ.ር)

84

አዲስ አበባ: ጥር 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት ጫና ለሉዓላዊነቷ ባላት አቋም እና በምሥራቅ አፍሪካ የምታደርገው ሰላምን የመሻት ፍላጎት የቀጣናውን አይደፈሬነት ትገዳደራለች በሚል እንደኾነ የዘርፉ ተንታኞች ይናገራሉ።

ከዓለም ሕዝብ ቁጥር 16 ነጥብ 7 በመቶ ሕዝብ የሚኖርባት አፍሪካ በጸጥታዉ ምክር ቤት ተገቢውን ውክልና አላገኘችም በሚል የፍትሐዊነት ጥያቄ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ማንሳቷም አንዳንድ ምዕራባውያንን እንዳላስደሰተ ተደጋግሞ ይነሳል።

አፍሪካዊያን ለነጻነታቸዉ እንዲታገሉ ኢትዮጵያ በር እንደከፈተችው ኹሉ በእጅ አዙር ቀኝ አስተዳደር ሥር እንዳይወሉም በጽኑ አቋሟ ተጠቃሽ ናት፡፡ ያላትን ሊነጥቋት የምትፈልገውንም ሊነሷት የኹልጊዜ የቤት ሥራ አድርገው የያዙት አንዳንድ ምዕራባዊያን የአፍሪካ መዲናነቷን ሊቀሙ ያላደረጉት ጥረት አልነበረም።

ኢትዮጵያ የጠላቶቿን ፍላጎት በማክሸፍ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን ማስተናገዷ ለተፅዕኖ የማትበገር እና ሰላሟን ማስከበር በእጇ እንደሆነ አሳይታበታለች ሲሉ የዓለምአቀፍ ሕግ ባለሙያ ዘላለም ሞገስ (ዶ.ር) ተናግረዋል፡፡

የጉባዔው በሰላም መጠናቀቅም የኢትዮጵያን ተጽእኖ ፈጣሪነት ማቀጨጭ መሪ እቅዳቸው ያደረጉት አንዳንድ ምዕራባዊያን የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫን ከኢትዮጵያ እንዲነሳ ያደረጉት ጥረት እንዲመክን አድርጎታል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን ኹሉ ውጣ ውረድ አልፋ 35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን በሕብረቱ መቀመጫ ማካሄድ መቻሏ ልክ እንደትላንቱ ምንም ችግር እንደማይበግራት እና ሰላም እና ጸጥታዋን ማስከበር እንደምትችል አሳይታበታለች ይላሉ የዓለምአቀፍ ሕግ ባለሙያ ዶክተር ዘላለም ሞገስ።

ኢትዮጵያ አይደለም በሰላም ጊዜ ችግር ውስጥም ኾና እንኳን ለአፍሪካዊያን መሰረት እንደኾነች እና አፍሪካዊያንን መሰብሰብ እንደምትችል አሳይታለች ያሉት ዶክተር ዘላለም በጠላቶቿ ዘንድ አፍሪካዊያን ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለውን ነባራዊ ኹኔታ በአካል ተገኝተዉ እንዳይረዱ ሲያደርጉት የነበረዉን የሴራ ውጥን አምክናበታለች ባይ ናቸው።

ዘጋቢ:- በለጠ ታረቀኝ -ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“35ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በሰላም፣ በስኬት፣ በወንድማማችነትና በትብብር መንፈስ ተጠናቋል” የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ
Next articleፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴና የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ የተፈናቀሉ ወገኖችን ጠየቁ።