
አዲስ አበባ፡ ጥር 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ ሰጥቷል።
35ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በሰላም፣ በስኬት፣ በወንድማማችነትና በትብብር መንፈስ ተጠናቋል፤ ለዚህም ለከተማችን ሕዝብና የፀጥታ አካላት ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል መግለጫውን የሰጡት የከተማ አስተዳደሩ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ፡፡
የከተማ አሰተዳደሩ የ6ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መደረጉን የጠቀሱት ኃላፊው የሴክተር መሥሪያ ቤቶች የመፈጸም አቅምና ያሉባቸውን ክፍተቶች ለመሙላት የሚያስችል የልምድ ልውውጥ ተገኝቷልም ብለዋል።
የአመራር አቅም ማጎልበት የሚያስችል ስልጠና ተሰጥቷል፤ ማኅበረሰብን ማገልገል የሚያስችል ትሁትና አገልጋይነት የተላበሰ አመራር ለመፍጠር መመረጥ ተለውጦ ለመለወጥ በሚል መሪ ሐሳብ ወይይት አድርገናል ብለዋል።
በካቢኔ ከተወሰኑ ውሳኔዎች መካከል የቻይና አፍሪካ የቀርቀሃ ሠርቶ ማሳያና ስልጠና ማዕከል ግንባታ ቦታ መፈቀዱንና ወጪውም በቻይና መንግሥት የሚሸፈን መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በአዲስ አበባ ማዕከሉ መገንባቱ በሁለቱ ሀገራት የእህትማማችነት በተለይም ደግሞ የባህል፣ የዲፕሎማሲ እና የቱሪዝም ዘርፉን ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።
የባህል ማዕከሉ በቻይና መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የሚገነባ ነው፤ ይህም ለቻይና አፍሪካ ትብብር ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በማየት የተፈቀደው ነው ብለዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በከተማው ያሉ የ13 የአፍሪካ ሀገራት ቦታ የሊዝ እዳቸው ተሰርዞ እንዲመለስላቸው መወሰኑም ተገልጿል፡፡
ዘጋቢ፡- ድልነሳ መንግስቴ -ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/