
ጥር 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ ዛሬ ሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ ፕሬዚዳንቷንና ምክትል ዋና ጸሐፊዋ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሱማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሌሎች የተመድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በቆይታቸውም በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ተፈናቅለው በቀብሪበያህ አካባቢ የሚገኙ ዜጎችን እንደሚመለከቱና ከነዋሪዎቹ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
ምክትል ዋና ጸሐፊዋ ትናንትም በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ በሽብር ቡድኑ ጥቃት ከደረሰባቸው ወገኖች ጋር ተወያይተዋል።
በአሸባሪው የጅምላ መቃብር የተፈጸመበትን እና የወደመውን የኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ማስልጠኛ ኮሌጅ ተመልክተዋል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/