የዚያ ዘመን ቅርሶች በዚህ ዘመን አይጠፉም!

211

ባሕር ዳር፡ መስከረም 29/2012 ዓ/ም (አብመድ) በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ታሪካዊ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ቅርሶች ይገኛሉ፤ ነገር ግን ቅርሶቹ በተለያዩ ምክንያቶች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ በተፈጥሯዊ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖና አንዳንዶቹ በዕድሜ ምክንያት ለብልሽት ተዳርገዋል፡፡

የዓለም ቅርስ የሆኑት የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደር አብያተ መንግሥታትና ሌሎችም ጥንታዊ መስጅዶችና ገዳማት በእርጅና ምክንያት እየተጎዱ ይገኛሉ፡፡

እነዚህን ቅርሶች ከተሠሩበት ዘመን ከዚህ እንደደረሱት ሁሉ ለቀጣዩ ትውልድም ለማሸጋገር እንዲቻል የአማራ ክልል የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት ፈንድ ጽሕፈት ቤት የድጋፍ ማሰባሰቢያ መንገዶችን አዘጋጅቷል፡፡

ከድጋፍ ማሰባሰቢያ መንገዶቹ አንዱ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ከሁሉም ዜጎች ድጋፍ መቀበል ነው፡፡ ስለሆነም ለክልሉ ቅርሶች መጠበቅ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚፈልጉ ሁሉ በ6122 ላይ ‹Ok› ብለው አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ በአንድ ጊዜ ሁለት ብር ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡

የአማራ ክልል የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት ፈንድ ጽሕፈት ቤት፡፡

Previous articleየጎንደር አብያተ መንግሥታት ጥገና ጥቅምት 3 ቀን 2012ዓ.ም ይጀመራል፡፡
Next articleቺርቤዋ-30-1-2012-1