ኢትዮጵያ እና ብሩንዲ በወታደራዊና በኢኮኖሚ መስክ በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

168

ጥር 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ብሩንዲ በወታደራዊና በኢኮኖሚ መስክ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

የኹለቱ ሀገራት ስምምነት ለቀጠናው ሰላምና ልማት ፋይዳው የጎላ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከብሩንዲው ፕሬዚዳንት ኤቬሪስት ንዳይሺሚዬ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይታቸውም ሀገራቱ በወታደራዊ፣ ኢኮኖሚ እና በሌሎች የልማት መስኮች ላይ በጋራ መሥራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ መሪዎቹ በውይይታቸው በተለይ በወታደራዊና በኢኮኖሚ መስክ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ በግብርናው መስክ ከፍተኛ እምርታ እያስመዘገበች መኾኑን መግለጻቸውንም ነው የጠቆሙት፡፡

በተለይ የበጋ መስኖ የስንዴ ልማት ላይ ኢትዮጵያ ከፍተኛ መሻሻል እያስመዘገበች መኾኑንም እንዲሁ፡፡

በዚህም ብሩንዲ ከኢትዮጵያ የግብርና መስክ በርካታ ልምድ መቅሰም እንደምትችልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውንም አውስተዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከራሷ አልፎ ለአከባቢው ሀገራት ፋይዳው የጎላ የሆነውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር በስኬት እየተገበረች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ይህም የቀጣናው ሀገራትን ተፍጥሯዊ ምህዳር በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውና ተሞክሮው ወደ ሌሎች ሀገራት መስፋት እንዳለበትም አብራርተዋል ነው ያሉት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ፡፡

የብሩንዲው ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ከኹለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን አስታውሰው፤ አሁን ላይ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ለውጥ ውስጥ መሆኗን መታዘባቸውን ተናግረዋል ነው ያሉት፡፡

ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ውስጣዊና ውጫዊ ችግር ተቋቁማ የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤን በሰላም ማካሄድ መቻሏን መናገራቸውንም ነው የገለጹት፡፡

ለዚህ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መንግስት ከፍተኛ ሚና መጫወቱንም ነው የተናገሩት፡፡

በቀጣይ የቡሩንዲ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በግብርናው መስክ ልምድ እንደሚቀስምም ፕሬዚዳንቱ ማረጋገጣቸውን ዶክተር ለገሰ ቱሉ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያና ብሩንዲ የቆየ መልካም ግንኙነት ያላቸው ሀገሮች ሲኾኑ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን በጋራ በመስራት ይታወቃሉ።

በሶማሊያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ የሰላም አስከባሪ ኃይል በማሰማራት ላቅ ያለ ሚና አላቸው፡፡

ፕሬዚዳንት ኤቬሪስት ንዳይሺሚዬ እ.አ.አ በ2020 ሰኔ ወር ላይ ወደ ስልጣን ሲመጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ ኢትዮጵያ ከቡሩንዲ ጋር በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸው ይታወሳል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴም ባለፈው ዓመት የካቲት ወር በቡሩንዲ የኹለት ቀናት የሥራ ጉብኝት በማድረግ የኹለቱን ሀገራት ትብብር ይበልጥ በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይ ከሀገራቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸው ይታወቃል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ኮምቦልቻ ገቡ።
Next articleየኢፌዴሪ ፕሬዚዳንትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ ጅግጅጋ ገቡ።