
ጥር 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የገቢዎች ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም የመንፈቅ ዓመት ብቻ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
“የሕዝብን ሀብት ለሕዝብ” በሚል መርህ ድጋፍ መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከ1 ቢሊዮን 105 ሚሊየን 808 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ለሕዝብ በቀጥታ ማድረሱን አስታውቋል፡፡ በመንፈቅ ዓመቱ ከ1 ቢሊዮን 126 ሚሊየን 931 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ነው የገለጸው፡
የተደረጉት ድጋፎች በዋነኝነት በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች፣ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በጦርነቱ ለተሳተፉ ዘማቾች፣ ለበጎ አድራጎት ማኅበራት፣ በሥራ ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው፤ በህመም እና ችግር ላጋጠማቸው የተቋሙ ሠራተኞች፣ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ለአማራ እና ለአፋር ክልሎች እንዲሁም ለሶማሌ ክልል አደጋ ስጋት መሆኑም ታውቋል፡፡
የተደረገው ድጋፍ የገንዘብና የቁሳቁስ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች ከደምወዛቸው በማዋጣትና ደም በመለገስ አርዓያነት ያለው ተግባር መፈጸማቸውም ተገልጿል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን የፀረ-ኮንትሮባድ መከላከል ሥራውን አጠናክረው በመሥራት ለመንግሥት ገቢ መደረግ ያለበትን ገቢ እያደረጉ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡ በሕገወጥ የኮንትሮባንድ ዝውውሩ የሚያዙና የሕዝብ ሀብት የሆኑ የተለያዩ ቁሳቁስ የሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ችግር ለአጋጠማቸው አካባቢዎችና የማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡
በኮንትሮባንድ የተያዘ ቁሳቁስ ለኹሉም ክልሎች፣ ለኹለቱ ከተማ መሥተዳድሮች፣ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ማኅበራት እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ግዳጅ ላይ ለሚገኘው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ መደረጉን አስታውቋል፡፡
የተደረገው ድጋፍ የሕዝብን ሀብት ለሕዝብ እንደሚድረስ የሚያሳይ በመሆኑ የተደሰትንበትና እና የኮራንበት ተግባር ነው ብሏል ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ፡፡ መልካም ተግባሩን ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
የማኅበራዊ ኃላፊነት ተግባሩ እንዲከናወን የገቢዎች ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች፣ አጋር አካላት እንዲሁም ለዚህ መልካም ሥራ ተባባሪ ለነበሩ ኹሉ ምሥጋና ይድረሳቸው ብሏል ገቢዎች ሚኒስቴር፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/