
አዲስ አበባ: ጥር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር እና የሴኔጋል ኘሬዚዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በተሳካ ኹኔታ እንዲጠናቀቅ እና በኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝ ምክንያት የተጋረጠበትን ስጋት ተቋቁሞ እንዲካሄድ በመቻሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ምሥጋና አቅርበዋል።
ሊቀመንበሩ በርሳቸው የመሪነት ዘመን አህጉሪቷን በኢኮኖሚና መሠረተ ልማት ለማስተሳሰር እንደሚሠሩም ገልፀዋል።
35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ለኹለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ተጠናቅቋል።
በመዝጊያ መርኃግብሩም የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር እና የሴኔጋል ኘሬዚዳንት ማኪ ሳል በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዕክል ገጥሞት የነበረውን የሕብረቱ ጉባኤ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በአካል በመገኘት ውጤታማ ውይይት ማድረግ እንዲቻል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ላደረጉት አቀባበል እና ስኬታማ ዝግጅት አመስግነዋል።
በርሳቸው የሊቀ-መንበርነት ዘመን አህጉሪቱን በኢኮኖሚ፣ በፓለቲካ እና በመሠረተ ልማት ከዳካር እስከ ሞምባሳ እንዲሁም ከኬኘ ቨርዴ እስከ ካይሮ ለማስተሳሰር እሠራለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ኃይለኢየሱስ አለልኝ- ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/