❝35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በኹለተኛ ቀን ውሎው ሽብርተኝነትን መከላከልና የአጀንዳ 2063 ዕቅድን ለማሣካት በተከናወኑ ሥራዎች ላይ መክሯል❞ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

89

አዲስ አበባ: ጥር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በኹለተኛ ቀን ውሎው ሽብርተኝነትን መከላከልና የአጀንዳ 2063 ዕቅድን ለማሣካት በተከናወኑ ሥራዎች ላይ መምከሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።

ጉባኤው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አሠራር ሪፎርም እንዲደረግ በሚጠይቀው ሐሳብ ላይም መምከሩን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ከጀመረ ኹለተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ 35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ስለመከረባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች በተመለከተ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

ጉባኤው ከጠዋት በፊት በነበረው ውሎ አጀንዳ 2063 ፣ ሽብርተኝነት፣ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ሪፎርም እንዲደረግ የሚጠይቅ ሐሳብ፣ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ጉዳይ እና ተቋማዊ ለውጥን የተመለከቱ ጉዳዬች ውይይት የተደረገባቸው ሐሳቦች እንደሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል።

በጉባኤው ትኩረትን ከሳቡት ጉዳዬች መካከል አጀንዳ 2063 ለማሣካት የተደረጉ ጥረቶች በኮትዲቯር ኘሬዚዳንት ኦላሳኔ ኦታራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በቀጣይ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ጉዳዮች መሠራት ስላለባቸው ጉዳዬች አቅጣጫ ተቀምጧል። በጉባኤው ማጠቃለያም ውሳኔ ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል ነው የተባለው።

በሌላ በኩል ሽብርተኝነትን እና በፅንፈኝነት የሚከሰቱ ግጭቶችን የተመለከተው የሕብረቱ ሪፖርት በአልጀሪያው ኘሬዚዳንት አብዱልመጂድ ቴቡኔ በኩል ቀርቦ እንደ አህጉር ያለበትን ኹኔታና ቀጣይ ለመከላከል መከናወን ባለባቸው ጉዳዬች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።

የሕብረቱ የፋይናንስ ጉዳይን በተመለከተም ውይይት የተደረገ ሲኾን የስደት ጉዳይን በተመለከተ የሞሮኮው ንጉሥ ሞሐመድ ስድስተኛ በኩል ቀርቦ ውይይት መደረጉን ቃል ዐቀባዩ ገልፀዋል።

ሌላው የሕብረቱ ጉባኤ በትኩረት የመከረበት ጉዳይ የፀጥታው ምክር ቤት አሠራርን እና አወቃቀርን ሪፎርም እንዲደረግ መክሯል፤ ይህን ጉዳይ አፍሪካውያን ብቻ ሳይኾን አንዳንድ የእስያ ሀገራትና ሌሎች ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገራት ፍላጎት ጭምር በመኾኑ ከነኚህ ሀገራት ጋር በመናበብ መሥራት እንደሚገባም ተጠቁሟል።

ጉባኤው ከዚህ በተጨማሪ ነፃ የንግድ ቀጣና፣ የተቋማት ሪፎርምን እና ሌሎች ጉዳዬችን ሪፖርት አድምጦ መክሯል።

ጉባኤው ከነዚህ አጀንዳዋች በተጨማሪ የተለያዩ ሹመቶችንም መሪዎቹ ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- ኃይለኢየሱስ አለልኝ -ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በኹለትዮሽና የአፍሪካ ዘላቂ ጥቅም ላይ ያተኮረ ነው❞ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Next articleጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኬኒያ እና ሴኔጋል ፕሬዚዳንቶች ጋር በኹለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መከሩ።