❝ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በኹለትዮሽና የአፍሪካ ዘላቂ ጥቅም ላይ ያተኮረ ነው❞ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

171

ጥርጣሬን 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በሁለትዮሽና የአፍሪካ ዘላቂ ጥቅም ላይ ያተኮረ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከ35ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ በተጓዳኝ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ውይይት አስመልክቶ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ከዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ጋር በኹለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ኹለቱ መሪዎች አፍሪካ አኹን ካሉባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንድትወጣ ማድረግ በሚቻልባቸው የመፍትሔ አማራጮች እንዲሁም የአፍሪካ ድምጽ በዓለም መደመጥ በሚችልበት ኹኔታ ላይ መክረዋል።

የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ፤ በውይይታቸው ኢትዮጵያ ከገባችበት ጫና ለመውጣት እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቀዋል።

ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ እንደሚያስፈልግና ለዚህ ኹሉም መዘጋጀት እንደለበት መናገራቸውን ዶክተር ለገሰ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የአፍሪካ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት በአህጉራዊ መፍትሔዎች መሆኑንም መሪዎቹ አንስተው መክረዋል ብለዋል።

የግብርና ልማት የአፍሪካን ችግር መፍቻ ዋንኛ መንገድ በመኾኑ አፍሪካውያን በተቀናጀ መልኩ መሥራት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

ከኢትዮጵያ ግብርና በተለይም ከበጋ መስኖ ልማት ዚምባቡዌ ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግና ለዚህም አንድ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንድትልክ መሪዎቹ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሐመዱ ቡሃሪ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ዶክተር ለገሰ ገልጸዋል።

ኹለቱ መሪዎች የአፍሪካን መጻዒ እድል የተሻለ ለማድረግ ከድህነትና ኋላቀርነት ማላቀቅ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተነጋግረዋል።

ናይጄሪያ ለፓን አፍሪካኒዝም መጠናከርና ለአህጉሩ ኹለንተናዊ ተጠቃሚነት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራት ተነስቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ትናንትም ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር በኹለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ይታወቃል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በግፍ የተጨፈጨፉ ወገኖች የጅምላ መቃብሮችን በኮምቦልቻ ከተማ ተመለከቱ።
Next article❝35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በኹለተኛ ቀን ውሎው ሽብርተኝነትን መከላከልና የአጀንዳ 2063 ዕቅድን ለማሣካት በተከናወኑ ሥራዎች ላይ መክሯል❞ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ