የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በግፍ የተጨፈጨፉ ወገኖች የጅምላ መቃብሮችን በኮምቦልቻ ከተማ ተመለከቱ።

160

ጥር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በኮምቦልቻ ጭፍጨፋ የፈጸመባቸው ንጹሐን ወገኖች የጅምላ መቃብሮችን እና በኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የደረሰውን ውድመትና ዘረፋ ተመልክተዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱ ሁሴን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በግፍ የጨፈጨፋቸውን ንጹሐን በጅምላ ስለመቅበሩና በኮሌጁ ላይ ስለተፈጸመው ኹለንተናዊ ውድመትና ዘረፋ ለምክትል ዋና ጸሐፊዋ ገለጻ አድርገዋል።

ምክትል ዋና ጸሐፊዋ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ከአመራሩና የተለያየ ጥቃት ከደረሰባቸው ሴቶች፣ ሕጻናትና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋርም ተወያይተዋል።

ምክትል ዋና ጸሐፊዋ በሽብር ቡድኑ የወደሙ ሌሎች ተቋማትንም ተዘዋውረው ይመለከታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በምልከታው የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀምበር፣ የክልሉ ዋና አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከናይጄሪያ እና ዚምባቡዌ ፕሬዚዳንቶች ጋር በኹለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ።
Next article❝ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በኹለትዮሽና የአፍሪካ ዘላቂ ጥቅም ላይ ያተኮረ ነው❞ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት