
አዲስ አበባ: ጥር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የአህጉሩ ገዳይ በሽታ የኾነውን የወባ በሽታ ለመከላከል ቁርጠኝነታቸውን እያሳዩ መሆኑን የኬንያ ኘሬዚዳንት እና ወባን ለመከላከል የተቋቋመው የሕብረቱ የወባን መከላከል ጥምረት መሪ ኡሁሩ ኬኒያታ ገልጸዋል።
ኘሬዚዳንቱ በሪፖርታቸው እንዳመላከቱት የ “ዜሮ ወባ” ዘመቻን በርካታ የሕብረቱ አባል ሀገራት ተቀብለው እየተንቀሳቀሱ ነው። ኾኖም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋት ዘመቻውን አሰቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል።
እርሳቸው በሚመሩት የዜሮ ወባ ዘመቻ 15 ያክል አባል ሀገራት በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጨረሻ ምክር ቤት አቋቁመው ዘመቻውን በፋይናንስና ሌሎች ድጋፎች ለማገዝ ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ገልጸዋል።
ኘሬዚዳንቱ የፀረ ወባ ክትባትን አስመልከተው በሰጡት ሐሳብም ከአራት የማያንሱ ሀገራትም አዲሱን እና የተሻሻለውን የፀረ- ወባ ክትባት ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት መስጠት የጀመሩ መሆኑን ገልፀው ሌሎች አባል ሀገራትም እንዲጀምሩ ጠይቀዋል።
የተጀመረውን የሕብረቱ የዜሮ ወባ ዘመቻ ለማሳለጥና ውጤታማ ለማድረግም ቀጣናዊ የንግድና ሌሎች ማኅበራዊ ጥምረቶችን መጠቀምም እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህን ዘመቻ ውጤታማ ለማድረግም የዓለምአቀፉን ማኅበረሰብ ትብብርና ድጋፍም ጠይቀዋል።
ኘሬዚዳንት ኡሁሩ የአፍሪካ መሪዎች የ”ዜሮ ወባ” ዘመቻን በፋይናንስና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች እንዲያግዙም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ኃይለኢየሱስ አለልኝ- ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/