
ጥር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው እና ወራሪው የትግራይ ቡድን በትምህርት ተቋማት ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወቃል። የሐራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በወራሪው ቡድን ከተጎዱት የትምህርት ተቋማት አንዱ ነው።
የግሎባል አሊያንስ መሥራች እና ኃላፊ አርቲስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ እንዲሁም የአማራ ልማት ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፋንታ ትምህርት ቤቱን ተመልክተዋል። ጉዳት የደረሰበትን ትምህርት ቤት የተሻለ አድርገው እንደሚሠሩት ተናግረዋል።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለይም በፍሎሪዳና በሚኒሶታ ነዋሪ የኾኑ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ይህንን ትምህርት ቤት ከነበረበት ከፍ አድርጎ ለመሥራት ርብርብ እንዲያደርጉ አርቲስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ጥሪ አቅርበዋል።
ለሐራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደረጃቸውን የጠበቁ መማሪያ ክፍሎች እንደሚሠሩ የገለፁት የአልማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፋንታ ትምህርት ቤቱን ከግሎባል አሊያንስ ጋር በመተባበር እንደሚገነባውና ቁሳቁስም እንደሚያሟላ ቃል ገብተዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋሁን ባታብል ❝አልማና ግሎባል አሊያንስ የሐራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን መልሶ ለመገንባት የጀመራችሁት ውጥን ተጠናቅቆ መልሰን እንደምንገናኝ እርግጠኛ ነኝ❞ ብለዋል።
ለሐራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የትምህርት ማስጀመሪያ የመማሪያ ቁሳቁስ የአማራ ልማት ማኅበር ለግሷል።
ዘጋቢ:- ካሳሁን ኃይለሚካኤል–ከሐራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/