ኢትዮጵያ እና ሩስያ በተመድ እና ሌሎች ባለብዙ ግንኙነት መድረኮች ላይ ያላቸውን ቅንጅት ለማጠናከር ተስማሙ።

338

ጥር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከ35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከሩስያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካኤል ቦግዳኖቭ ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው ፈርጀ-ብዙ የኾነውን የሁለቱን ሀገራት ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ኹኔታ ላይ መክረዋል።

በኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ግብርና እንዲሁም ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች በኹለቱ አገራት ትብብር ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚከናወኑ ተስፋ ሰጪ ፕሮጀክቶችም ተወያይተዋል።

የጋራ ጥቅምን በሚመለከቱ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ኹነቶች ዙሪያም ሐሳብ ተለዋውጠዋል። በዚህም በተመድ እና ሌሎች ባለብዙ ግንኙነት መድረኮች ላይ ያላቸውን ቅንጅት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

በአፍሪካ የሚያጋጥሙ ግጭቶች እና ቀውሶችን በዓለም አቀፍ ሕግ እና የተመድ ቻርተር አግባብ መፍታት እንደሚገባም መግባባት ላይ ደርሰዋል።

በ2022 ስለሚካሄደው 2ኛው የሩስያ-አፍሪካ ጉባኤ ዝግጅትም መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

የሩስያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካኤል ቦግዳኖቭ የሩስያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የመካከለኛው ምሥራቅ እና የአፍሪካ ልዩ ተወካይም ናቸው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝ወደ ጎንደር እና ባሕር ዳር የበረራ መስተጓጎል አጋጥሟል❞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
Next articleግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያውያን መብት ከአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ጋር በመተባበር በሐራ ከተማ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልሶ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ።