“ለአህጉራዊ የምጣኔ ሀብት ውህደት ዓላማ መሳካት የፋይናንስ ግኝት ማብዛት ወሳኝ መኾኑ ተመክሮበታል” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

111

ጥር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትናንት በተጀመረው 35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በስፋት በዝግ ስለመከረባቸው ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአፍሪካ ወቅታዊ የሰላም እና ፀጥታ ሪፖርት፣ የኮሮናቫይረስ ወቅታዊ ኹኔታ እና ተዛማች ተፅዕኖ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ በአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ውህደት ዙሪያ ያለውን ወቅታዊ ሪፖርት ቀርቧል ነው ያሉት።

በሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአህጉሪቷ እየታየ ያለው ሕገ መንግሥታዊ ያልሆኑ የሥርዓት ለውጦች መበራከታቸው ከሌሎች የሰላም እና ፀጥታ ችግሮች ጋር ተዳምረው ለአህጉሪቷ የደኅንነት ስጋት ደቅነዋል ነው የተባለው። ይህ አይነት አካሄድ ተቀባይነት የሌለው በመኾኑ ሊቆም እንደሚገባም ውይይት ተደርጎበታል።

በሌላ በኩል ውይይት የተደረገበት የኮሮናቫይረስ ተፅዕኖ ነው።

እንደ አምባሳደር ዲና ማብራሪያ በዚህ ጉዳይ መሪዎች ትኩረት የሰጡበት ክትባት ተደራሽ ላይ መሥራት እና በአፍሪካ ክትባት ለማምረት የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማበረታታት እና መደገፍ እንደሚገባ ነው።

በአፍሪካ ልማት ባንክ የቀረበው አህጉራዊ የምጣኔ ሀብት ውህደት ያለበት ደረጃ እንዳመላከተው ከኾነ ደግሞ ለዚህ ዓላማ መሳካት አሁንም የፋይናንስ ግኝት ማብዛት ወሳኝ መኾኑን መምከሩን አምባሳደር ዲና መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡ የፋይናንስ ግኝቱን በስፋት እንዲያፈላልግም የአፍሪካ ልማት ባንክን መደገፍ እንደሚያስፈልግ በመሪዎች ተመክሮበታል ነው ያሉት።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“አሚኮ በሕልውና ዘመቻው ማኅበረሰቡን በማንቃት የተሰጠውን ኀላፊነት ተወጥቷል”ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ
Next articleየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ሙሃመድ በአሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን የወደሙ ተቋማትን ለመመልከት አማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ ገብተዋል።