“አሚኮ በሕልውና ዘመቻው ማኅበረሰቡን በማንቃት የተሰጠውን ኀላፊነት ተወጥቷል”ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ

143

ባሕር ዳር: ጥር 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የአማራ ሕዝብ በአንድነት በመሆን ከኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹ ጋር በመሆን አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን እንዲፋለም ሚናው ከፍተኛ እንደነበር የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ገልጸዋል።

አሚኮ ማኅበረሰቡን በማንቃት የተሰጠውን ኀላፊነት መወጣቱን የገለጹት ርእሰ መስተዳድሩ የጋዜጠኞች ቅንጅታዊ ሥራም ከፍተኛ እንደነበር አንስተዋል።

ሚዲያው የአማራን ሕዝብ አንድነት የሚያጠናክር፣ ወጉን እና ባህሉን የሚያጎሉ እና ከሌሎች ሕዝቦች ጋር አብሮነቱ እንዲጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎችን መስራት ይገባዋልም ብለዋል።

በእውነት ላይ ተመስርቶ ተግቶ በመስራት አሚኮን ተመራጭ ማድረግ እንደሚገባም አንስተዋል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል።

ተጨማሪ ቻናሎችን በመክፈት እየተሠራ ያለው ሥራም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

አሚኮ ትክክለኛ፣ ሚዛናዊ እና ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ዘገባዎችን በማቅረብ የበለጠ ተመራጭ እንዲሆን መሥራት እንደሚገባም ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) አስገንዝበዋል።

የክልሉ መንግሥትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በዳግማዊ ተሰራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኅልውና ዘመቻው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን ለመደምሰስ በተደረግው ትግል አኩሪ ተግባር መፈጸሙን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ሙሉቀን ሰጥየ ገለጹ።
Next article“ለአህጉራዊ የምጣኔ ሀብት ውህደት ዓላማ መሳካት የፋይናንስ ግኝት ማብዛት ወሳኝ መኾኑ ተመክሮበታል” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ