አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኅልውና ዘመቻው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን ለመደምሰስ በተደረግው ትግል አኩሪ ተግባር መፈጸሙን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ሙሉቀን ሰጥየ ገለጹ።

90

ባሕር ዳር: ጥር 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለታታሪና ምስጉን ሠራተኞች የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር እያካሄደ ነው።
በመርሃ ግብሩ የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥየ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ባለፉት ወራቶች አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን ለመደምሰስ በተደረግው ትግል ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ብለዋል።

በሕልውና ዘመቻው አሚኮ ሕዝቡን ጠላቱን እንዲመክት፣ የኋላ ደጀን እንዲሆን በማነሳሳት፣ ትግሉን በስንቅ እንዲደግፍ በማድረግ እና የወገን ጦርን ተጋድሎ ግንባር ገብቶ በመዘገብ አኩሪ ተግባር ፈጽሟል ነው ያሉት።
ከሕግ ማስከበሩ ጊዜ ጀምሮ እስከ ህልውና ዘመቻው ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን የአሸባሪውን ትህነግ ሴራ በማጋለጥና ኢትዮጵያዊያን በጋራ እንዲታገሉት በማድረግ አሚኮ የፈጸመው ተግባር ታላቅ እንደሆነ ገልጸዋል።
አሚኮ ባለፉት ስድስት ወራቶች በሁሉም ቋንቋዎች መደበኛ ዝግጅቶችን በማጠፍ ሙሉ ትኩረቱን በህልውና ዘመቻው ላይ በማድረግ ሰፊ ስራ ሰርቷል ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው።
አሚኮን በቀጣይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተጽእኖ ፈጣሪ ሚዲያ ለማድረግ እየተሠራ እንደሆነም አብራርተዋል።
በመላኩ ሙሉጌታ
ኢትዮጵያን
እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝አፍሪካ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ ግብርናን ማዘመን ላይ ማተኮር አለባት❞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“አሚኮ በሕልውና ዘመቻው ማኅበረሰቡን በማንቃት የተሰጠውን ኀላፊነት ተወጥቷል”ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ