❝አፍሪካ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ ግብርናን ማዘመን ላይ ማተኮር አለባት❞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

119

አዲስ አበባ: ጥር 28/ 2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ አህጉርን የሥርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፣ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ መልዕክት 35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ በሕብረቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባኤውን የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ተጀምሯል። የኮሮና ቫይረስ እና ሽብርተኝነት አፍሪካን የፈተኑ ችግሮች እንደነበሩ አንስተዋል።
ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አፍሪካዊያን ስለችግራችን በአካል ተገናኝተን መምከር እንዳንችል እንቅፋት ነበር ብለዋል ሙሳ ፋኪ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የአፍሪካን የግብርና ልማት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። አፍሪካ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ ግብርናን ማዘመን ላይ ማተኮር እንዳለባት ጠቅሰዋል። የግብርና ምርት ይጨምር ዘንድ የአየር ንብረት ሚዛንን መጠበቅ መሠረታዊ እንደሆነም አንስተዋል። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ኢትዮጵያ በመሪነት የችግኝ ተከላ ተግባር ላይ አተኩራ እየሠራች እንደሆነ ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርቱን ሲያቀርቡ ኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ ገጥሟት እንደነበር እና ችግሩን በራሷ ጥረት መፍታት እንደቻለች፣ በውጭ ጣልቃ ገብነት በሀገሪቱ መረጋጋት እንዳይኖር ጥረት ሲደረግ እንደነበርም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ተሻግራ የሕብረቱ ጉባኤ እንዲካሄድ ማድረግ ችላለች ብለዋል።
የተመድ ዋና ጸሐፊ አቶኒዮ ጉቴሬዝ በጉባኤው በበይነ መረብ ባስተላለፉት መልዕክት አፍሪካ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ለማምጣት ኢንቨስትመንትን ማበረታታት እንዳለባት ጠቁመዋል።
የቀጣይ የዓለም ራስ ምታት ከአየር ንብረት ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮች በመሆናቸው አፍሪካዊያን አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ አበክሮ መሥራት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል። ሽብርተኝነት እና የሰላም እጦት ሌላኛው የአፍሪካዊያን ችግር እንደሆነ አንስተው ይሄን ለመፍታት አፍሪካዊያን የበሰለ እና ጠንካራ አመራር መፍጠር እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል።
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ፊሊክስ ሺሴኬዲ እና የቀጣዩ የሕብረቱ ሊቀመንበር ሆነው የሚመረጡት የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ዘጋቢ:- በለጠ ታረቀኝ -ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ።
Next articleአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኅልውና ዘመቻው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን ለመደምሰስ በተደረግው ትግል አኩሪ ተግባር መፈጸሙን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ሙሉቀን ሰጥየ ገለጹ።