በሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው የ2013 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

467

ጥር 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በፀጥታ ችግር ምክንያት የ2013 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ላልወሰዱ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ተላላኪዎቹ በፈጠሩት የፀጥታ ችግር ምክንያት በ2013 ዓም ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች በሁለተኛ ዙር ከጥር 24/2014 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናውን ሲወስዱ ቆይተዋል።
የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋርና በቤንሻንጉል ክልል በ189 የፈተና መስጫ ጣቢያዎች የተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና ካለምንም እንከን በሰላም መጠናቀቁን ተናግረዋል።
ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የፀጥታ አካላት፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች እና የክልል ትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ምሥጋናቸውን ማቅረባቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleጥር እና ቱሪዝም በአማራ
Next articleየፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሽታይ አዲስ አበባ ገብተዋል።