
ደባርቅ: ጥር 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር ለደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ብር የሚገመት የመድኃኒት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የማኅበሩ የሕክምና ባለሙያ እና ድጋፉን ያስረከቡት አቶ ባድማው ደሳለኝ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር በአማራ ክልል በኹሉም አካባቢዎች በመዘዋወር የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የጤና ተቋማት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
አቶ ባድማው ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ከደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ጋር በመነጋገር በሆስፒታሉ ያለውን የመድኃኒት እጥረት ለመቅረፍ ከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ብር የሚገመት የተለያዩ መድኃኒቶችን ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
ማኅበሩ በቀጣይም እገዛ የሚያስፈልጋቸውን የጤና ተቋማት በመደገፍ ማኅበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲኾን የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ መኩሪያው አማረ በበኩላቸው ድጋፉ ያለውን የመድኃኒት እጥረት የሚያቃልልና ለማኅበረሰቡ ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት እንድንሰጥ የሚያደርግ ነው ብለዋል። የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዳያስፖራዎች፣ድርጅቶችና የተለያዩ አካላት በሚያደርጉት ድጋፍ ጠቅላላ ሆስፒታሉ የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት እያቃለለ ለማኅበረሰቡ አገልግሎት እየሰጠ ነው ያሉት አቶ መኩሪያው የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ:- አድኖ ማርቆስ -ከደባርቅ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/