
ወልድያ: ጥር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ የወልድያና አካባቢዋ ተወላጆች ለወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ7 መቶ ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችንና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ድጋፍ አድርገዋል።
ማኅበሩን ወክለው ያስረከቡት ወይዘሪት ነፃነት ጌታዬ ይህ ድጋፍ የመጀመሪያቸው መሆኑን ገልፀው ማኅበራቸው አሁን የሆስፒታሉን ጎደሎዎች በመቃኘት ተጨማሪ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍስሃ የኋላ ማኅበሩ ያደረገውን ድጋፍ አመስግነው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሆስፒታሉ ካደረሰበት ውድመት አኳያ ተጨማሪ ድጋፎችን እንሻለን ብለዋል።
ዘጋቢ:–ካሳሁን ኀይለሚካኤል
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/