
አዲስ አበባ: ጥር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፍትሕ ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የመጀመሪው ግማሽ በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል:: ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የምርመራ እና የክርክር መዛግብት፣ የፍትሐብሔር፣ የሕግ ምክር፣ የሰብዓዊ መብት ማክበርና ማስከበር አፈጻጸም ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
ሚኒስትሩ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰዉ ክሳቸዉ የተቋረጠ ግለሰቦችን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ሪፖርቱን ያዳመጡት የምክር ቤቱ አባላት “በከፍተኛ የሽብር ወንጀል ተከሰው የታሠሩ ግለሰቦችን ክስ ማቋረጥ በድርጊቱ ጉዳት የደረሰባቸዉ ዜጎችን እንደመካድ አይቆጠርም ወይ?” ሲሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡
የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ አካላትን ክስ ማቋረጥ ያስፈለገዉ ሀገሪቱ የገጠማትን ሁለንተናዊ ቀውስ ለማርገብ ለሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ዉጤታማነቱ የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ተከሳሾቹ በእስር ከሚቆዩ ይልቅ መፈታታቸው ከሚያስገኘው የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ጥቅም አንጻር መኾኑን አብራርተዋል፡፡
የፍትሕ ሚኒስቴር በቀጣይ የሀገሪቱን የፍትሕ ስርዓት ወደ ፊት ያራምዳሉ ያላቸዉን የትኩረት አቅጣጫዎችንም ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡
በሀገሪቱ በተለያዩ ስፍራዎች በተፈጸሙ ግጭቶች እና በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተፈጸሙ ወንጀሎችን ምርመራ በጥራት እና በቅልጥፍና መምራት ከትኩረት አቅጣጫዎቹ መካከል መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡
ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ-ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/