ማዕድን ሚኒስቴር በአማራ ክልል በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

147

ባሕር ዳር፡ ጥር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ማዕድን ሚኒስቴር በአማራ ክልል በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። በድጋፉም የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ተበርክቷል፡፡

የቁሳቁስ ድጋፉ በጦርነቱ ምክንያት ዘረፋ እና ውድመት ለደረሰባቸው ተቋማት መልሶ ግንባታ የሚውል ነው ተብሏል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያደረገውን ድጋፍ ለክልሉ ያስረከቡት የማዕድን ሚኒስቴር የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር የሰውዘር ንጋቱ የተደረገው ድጋፍ የመጀመሪያ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የርእሰ መሥተዳድሩ ልዩ አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ክልሎች እና ተቋማት እያደረጉት ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleኢትዮጵያ በግብርና እና ቱሪዝም ዘርፎች ከሞሮኮ ጋር ጠንካራ ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
Next articleየተፈተነ ብርታት!